የዓለም የድህነት ዑደትን የማስቆም ዓላማን ያነገቡ 97 የቢዝነስ አመራሮችን ማስመረቁን ስታንፎርድ ሲድ አስታወቀ

በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል በነበረው ክብረ በዓል፣ በ2025 የትምህርት መርሃ ግብር ከሃያ ሁለት የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ 97 የቢዝነስ አመራሮችን ምረቃ ያከበረው ስታንፎርድ ሲድ፣ የዓለም የድህነት ዑደትን የማስቆም ዓላማን በማንገብ የሚንቀሳቀስ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የስታንፎርድ የድህረ ምረቃ የንግድ ትምህርት ቤት ፐሮግራም የሆነው ስታንፎርድ ሲድ በአፍሪካ፣ ኢንዶኔዥያ እና ደቡብ እስያ ካሉ ስራ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር ኢንተርፕራይዞች ህይወትን የሚቀይሩ ተግባራትን እንዲከውኑ የሚረዳ ነው ተብሏል።

በዚህም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሥልጠናዎችን እና ግብዓቶችን ለቢዝነስ መሥራቾች እና ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች እንደሚሰጡ፣ ይህም ገቢያቸውን ለማሳደግ፣ ሥራ ፈጠራን ለማበረታታትና በጎ ተጽዕኖ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚረዳ መሆኑ ተነግሯል።

በአዲስ አበባ የተካሄደው የምረቃ ሥነ ሥርዓት የአፍሪካ ሥራ ፈጣሪዎች ተፅዕኗቸው እያደገ መምጣቱን፣ እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት የሚጫወቱትን ትልቅ ሚና አጉልቶ እንደሚያሳይ ተጠቁሟል።

እስካሁን ድረስ 6መቶ85 ኩባንያዎች በፕሮግራሙ ተሳትፎ ማድረጋቸው የተገለፀ ሲሆን፤ ድርጅቶቹ አቅማቸውን ማጠናከር እንደተቻለ ተደራሽነታቸውም እንደሰፋ ተገልጿል፡፡

ከ2 ሺ 5 መቶ በላይ ቡድኖችን ያቀፈው ፕሮግራሙ በአርባ ሶስት ሀገራት ከ6 ሺ 1መቶ በላይ ተሳታፊዎች ያሉት ነውም ተብሏል፡፡

አዲስዓለም አበበ

ህዳር 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *