የቬንዚዌላው ፕሬዝዳንት “ማዱሮ አቋማቸውን ሳይለቁ በመቆየታቸው እና በሀገሩ ውስጥ ሊፈጸም ይችላል ተብሎ በሚገመተው ‘የጦር ወንጀል’ ምክንያት ውዝግብ እየተነሳ በመሆኑ ትራምፕ አጣብቂኝ ውስጥ መግባታቸው ተገልጿል፡፡
ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቬንዙዌላን ሥርዓት የመለወጥ ሂደት ወደ ስትራቴጂያዊ እና ፖለቲካዊ አጣብቂኝ የመቀየር አደጋ ላይ መሆኑ ተሰምቷል።
ትራምፕ በቅርቡ በካሪቢያን ባህር አካባቢ የቬንዙዌላ የጦር መርከቦች በመድኃኒት ዝውውር ላይ ተሰማርተዋል በሚል በተጠረጠሩ መርከቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ሰጥተዋል።
ፕሬዝደንት ማዱሮ በበኩላቸው የአሜሪካን ወታደራዊ እርምጃ ላይ ክስ ሰንዝረዋል።
ይህ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ወደ ከፍተኛ ወታደራዊ ግጭት ያመራል የሚል ስጋትንም ፈጥሯል።
ተቺዎች እና አንዳንድ የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ምንም እንኳን ዒላማዎቹ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ቢሆኑም፣ ማስረጃ ሳይቀርብ መርከቦችን ማጥቃት እና ሰዎችን መግደል የዓለም አቀፍ ህጎችን የሚጥስ ተግባር ነው፤ ይህ ደግሞ “የጦር ወንጀል” ሊያስብል ይችላል የሚል ስጋት አለ ብለዋል፡፡
ፕሬዝደንት ትራምፕ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ “ማዱሮ በቀላሉ መውጣት ከቻለ መልካም ነው ካልሆነ ግን በከባድ መንገድ ይሆናል” በማለት ቬንዙዌላን አስጠንቅቀዋል።
ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ የጦርነት ፍላጎት የለኝም ስለማለታቸውም ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ሱፊያን አህመድ
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
