የሰራተኞችን ጥቅም በማስጠበቅ ድምፃቸው እንዲሰማ የማድረግ ስራዎች በስፋት እየተሰራ ነው ሲሉ ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፤ በዚህ ዓመት ብቻ ወደ 3 ሺህ የሰራተኛ ማህበራትን ለማደራጀት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህንን ያሉት 37ተኛው ዓለም አቀፉ የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሔድ በጀመረበት ወቅት ነዉ።
ጉባኤው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አፍሪካ የመጣ ሲሆን፤ ከዛሬ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 2 ቀናት የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።
አቶ ካሳሁን ክፈተቶች ይኖራሉ ነገር ግን የሰራተኞችን መብት በመጠበቅ ረገድ ሰፊ እና የተሳኩ ስራዎችን በመስራታችን ምክንያት ነው 37ተኛውን አለም አቀፍ የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን ምክር ቤት ጉባኤ ለማዘጋጀት የታጨነው ብለዋል።
በመድረኩ የኢትዮጵያ የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን፤ የቻይና የሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን፤ ከሰሀራ በታችና የአፍሪካ ቀንድ ሠራተኞች ኮንፌዴሬሽን ክፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህን ዓለም አቀፍ መድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ጋር በመተባበር አዘጋጅቶታል፡፡
ሀና ሰይፉ
ህዳር 23/2018 ዓ.ም
