ከ600 ሚሊዮን ለሚበልጠው የአፍሪካ ሕዝብ የኤሌክትሪክ እጥረት መፍትሔ ለመስጠት፣ ያለመ ጉባኤ ሊካሄድ ነዉ

ከ600 ሚሊዮን ለሚበልጠው የአፍሪካ ሕዝብ የኤሌክትሪክ እጥረት መፍትሔ ለመስጠት፣ የአህጉሪቱን የኃይል ነፃነት ለማረጋገጥ እና ለአየር ንብረት ለውጥ ምላሾችን ለማስቀመጥ ያለመ ታላቅ ጉባኤ በሚቀጥለው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ሊካሄድ ነው።

የአፍሪካ ኃይል ጉባኤ (AEEC) ለእነዚህ ሦስት ወሳኝ ፈተናዎች ያለንን አቅም እንደ “የመጀመሪያ ነዳጅ” በመጠቀም ዘላቂ መፍትሔዎችን ለመስጠት ያለመ ነው።

ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ታኅሣሥ 10 እና 11 ቀን 2025 በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ዋና መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄዳል ተብሏል።

ጉባኤው በአፍሪካ የኃይል ኮሚሽን (AFREC)፣ የአፍሪካ ኅብረት (AU) ልዩ ኤጀንሲ፣ የሚመራ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

የጉባኤው ተሳታፊዎች በኃይል ሚኒስትሮች፣ በዓለም አቀፍ የልማት ባንኮች እና በግል ዘርፍ መሪዎች የተደገፈ ሰፊ ትብብር ይፈጥራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

ጉባኤው ኃይልን በቅልጥፍና መጠቀምን በማስቀደም፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የአፍሪካን የሀይል አቅም ለማረጋገጥ እንደሚያስችልም ተመላክቷል።

ጉባኤዉ የአፍሪካን የኃይል አቅም ከማሻሻል በተጨማሪም የኃይል ብክነትን በመቀነስ የካርቦን ልቀትን በመቆጣጠር የአየር ንብረት ምላሾችን ማጎልበት ላይ ትኩረት ያደርጋል።

በዚህም በኃይል ፍላጎት ላይ ከውጭ ጥገኝነትን በመቀነስ የኃይል ነፃነትን ማረጋገጥ የጉባኤው ማዕከላዊ ዓላማ ነው።

በቀጣዩ ሳምንት በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ የሚደረጉ ውሳኔዎች ለአፍሪካ የኃይል ዘርፍ የረጅም ጊዜ መመሪያ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ለዓለም አሰፋ

ህዳር 24/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *