“ሺሌጅ ፒፕል” የተባለው የአሜሪካ የዲስኮ የሙዚቃ ቡድን በ1970ዎቹ ዝነኛ የነበረውን ‘YMCA’ የተሰኘ የሙዚቃ ስራችውን እንደሚያቀርቡ ይጠበቃል። ዜማው በፕሬዝዳንት ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የዘመቻው መገለጫ ሆኖ ነበር።
48 ሃገራት የሚሳተፉበት የዓለም ዋንጫ የምድብ ድልድል ስነስርዓት አርብ በኬኔዲ ማዕከል ይከናወናል።
አንድሪያ ቦቼሊና ኒኮል ሸርዚንገርን የመሳሰሉ የሙዚቃው ዓለም ፈርጦችም ስራቸውን ያቀርባሉ።
የመድረኩ አጋፋሪዎች የኤሚ አዋርድ አሸናፊዋ ሄይዲ ክሉም እና ኮሜዲያኑ ኬሸን ሃርት ናቸው።
በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ከጁን 11 እስከ ጁላይ 19 ይከናወናል።
አቤል ጀቤሳ
ህዳር 24/2018 ዓ.ም
