የጸረ ተሕዋስያን መድሀኒቶች በጀርሞች መለመድ ለጤናው ዘርፍ ፈተና መሆኑ ተገለፀ

መድሃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ መውሰድ እና ያለ አግባብ መጠቀም የሰው፣ የአካባቢ እና የእንስሳት ጤና ላይ ያለው አሉታዊ ተፅእኖ እየጨመረ መምጣቱ ተገልጿል።

የህመም መንስዔ የሆኑ ጀርሞች በመላመድ የመቋቋም አቅም ስለሚያገኙ መድሃኒቶች አገልግሎት ላይ የመዋል ምጣኔያቸው እየቀነሰ እንደሚሄድ በጤና ሚኒስቴር የጸረ ተሕዋስያን መድሃኒቶች በጀርሞች መላመድ ተጠሪ ባለሙያ ወንድወሰን ሸዋረጋ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

ዜጎች ተገቢውን ምርመራ ባለማድረግ ያለማዘዣ ከመደብሮች የሚገዟቸው መድሃኒቶች ራሳቸውን ለበሽታ አጋልጠው መድሃኒቱ በአፋጣኝ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የአቅርቦት ማነስ እንዲከሰት ምክንያት እንደሚሆኑ ባለሙያው ገልፀዋል።

አስፈላጊ የሚባሉ መድሃኒቶችን ያለአግባብ መጠቀም ችግሩን ያሰፋዋል ሲሉም አፅንኦት ሰጥተዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በጸረ ተሕዋስያን መድሀኒቶች አጠቃቀም ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ፣ ግንዛቤን ለመፍጠር እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት የአምስት ዓመት የትግበራ ዕቅድን ወደ ስራ ማስገባቱን አንስተዋል።

በጤና ዘርፉ ላይ ከግብዓት አቅርቦት ጋር ተያይዞ ያለውን ክፍተት ከመሙላት ባሻገር የጉዳዩን አሳሳቢነት በዘላቂነት ለመፍታት ግንዛቤ የማስጨበጥ እና በትምህርት ስርዓት ውስጥ ለማካተት ጥረት እየተደረገ ስለመሆኑም ተነስቷል፡፡

ችግሩ በተጠቃሚዎች ብቻም ሳይሆን በጤና ባለሙያዎችም ክፍተት ጭምር እየተስፋፋ መሆኑ ፈታኝ እንዳደረገው ገልፀዋል።

ሐመረ ፍሬው

ታህሳስ 09/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *