ባንኩ “ንብ ሃላል” የተሰኘዉ የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሸሪዓ መርህ በመከተል ለ10 አመታት አገልግሎት ላይ መቆየቱ ተነግሯል።
ንብ ባንክ የዚህ አገልግሎት አዲስ መለያዉን በዛሬዉ እለት የአገልግሎቱን አስረኛ አመት ባከበረበት እለት አስተዋወቋል።
አገልግሎቱ ጅማሮዉን ካደረገበት አመት ጀምሮ የሸሪዓ መርህን ተከትሎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልፆል።
በ23 የባንኩ ቅርንጫፎች ሙሉ በሙሉ የዚህ የወለድ ነፃ አገልግሎቶች እየተሰጠባቸዉ እንደሚገኝ የባንኩ አመራሮች ተናግረዋል።
በተቀሩት ሌሎች የባንኩ ቅርንጫፎች በልዩ መስኮት አገልገሎቱን ለደንበኞቹ ማቅረቡን አይይዘዉ ገልፀዋል።
ከተመሠረተ ሀያ ስድስት አመታትን እንዳስቆጠረ የተናገረዉ ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ይህ አገልግሎት በታህሳስ 9 /2008 አ.ም ማስጀመሩን ተነግሯል።
የሸሪዓ ህግ አማካሪ ኮሚቴ በማቋቋም አገልግሎቱን ለአስር አመታት መስጠቱን የኮሚቴዉ የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር መሀመድ ዘይኑ ተናግረዋል።
ባንኩ በዛሬው እለት የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጥበትን ንብ ሃላል የተሰኘ አዲስ አርማ አስተዋውቋል።
ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ከ80 በላይ የአለም አገራት እየተገለገሉበት ያለ አሰራር ሲሆን 6 ትሪሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚንቀሳቀስበት የፋይናንስ ዘርፍ እየሆነ መምጣቱ ተነግሯል።
ቁምነገር አየለ
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
