የተባበሩት አረብ ኤምሬትሶች “ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለልማት” የተሰኘ የአፍሪካ ሃገራትን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፕሮጀክቶች የሚደግፍና በገንዘብ የሚያግዝ አንድ ቢሊየን ዶላር ዋጋ ያለው ኢኒሼቲቭ አስጀምራለች።
ኢኒሼቲቩ ዲጂታል መሰረተ ልማቶችን በማጎልበትና የመንግስት አገልግሎትና ምርታማነትን በማሳደግ የአህጉሩን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገት ለማገዝ የታለመ ነው።
የአቡ ዳቢው ልዑል ሼህ ካሊድ ቢን ሞሃመድ ቢን ዛዪድ አል ናህያን ይህንን ይፋ ያደረጉት በG20 ጉባዔ ነው።
ኢኒሼቲቩን ተግባራዊ እንዲያደርግ ሃላፊነት የተሰጠው የአቡ ዳቢ ኤክስፖርት ቢሮ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትሶች የውጪ እርዳታ ኤጀንሲ ጋር በመተባበር ነው።
ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም
