አንድ የሩስያ ጄኔራል በሞስኮ መኪና ላይ በተጠመደ ቦምብ ተገደሉ

አንድ የሩሲያ ጄኔራል በሞስኮ መኪና ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት መሞታቸዉን የሀገሪቷ ባለስልጣናት አስታዉቀዋል።

የሩስያ መርማሪ ኮሚቴ ሌተናል ጀነራል ፋኒል ሳርቫሮቭ ዛሬ ማለዳ ላይ በመኪና ስር በተጠመደ ፈንጅ ህይወታቸዉ ማለፉን ይፋ አድርጓል፡፡

በጥቃቱ የተገደሉት የ56 አመቱ ሳርቫሮቭ የጦር ሃይሎች ኦፕሬሽን ማሰልጠኛ መምሪያ ኃላፊ እንደነበሩ ኮሚቴው ገልጿል።

መርማሪዎቹ እንደተናገሩት ቦምቡ የተጠመደው በዩክሬን የስለላ ድርጅት ተሳትፎ ነው፤ ነገር ግን ስለመረጃው ዩክሬን አስተያየት አልሰጠችም።

ጥቃቱ የደረሰው በሩሲያ ዋና ከተማ በስተደቡብ የሚገኝ አንድ አፓርታማ አቅራቢያ በሚገኝ የመኪና ማቆሚያ ሲሆን፤ ጉዳዩን በጥለቀት ለማጥራት መርማሪዎች ወደቦታው ተልከዋል፡፡

ከስፍራው የወጡ ምስሎች በመኪና ማቆሚያ ቦታ ላይ በሮቹ የተገነጣጠሉ ነጭ መኪና በሌሎች ተሽከርካሪዎች ተከቦ ያሳያሉ፡፡

በየካቲት 2022 ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ለሙሉ ወረራን ከጀመረች አንስቶ በርካታ ወታደራዊ ባለስልጣናት በሩሲያ ዋና ከተማ ኢላማ ተደርገዋል፡፡

ጄኔራል ያሮስላቭ ሞስካሊክ በሚያዝያ ወር ሞስኮ ውስጥ በመኪና ላይ በተፈፀመ የቦምብ ጥቃት የተገደሉ ሲሆን፤ ጄኔራል ኢጎር ኪሪሎቭ በታህሳስ 2024 በሞተር ሳይክል ውስጥ የተጠመደ መሳሪያ በመፈንዳቱ ህይወታቸው ያለፈ ባለስልጣናት መሆናቸዉን ቢቢሲ አስታዉሷል፡፡

ሀና ሰይፉ

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *