ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር የሳህል ቀጣናዊ ኃይል አቋቋሙ

የማሊ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አሲሚ ጎይታ በባማኮ በሚገኝ የአየር ኃይል ካምፕ የሳህል አገራትን የተባበረ ኃይል ምስረታ በሚያበስረው ስነ-ስርዓት ላይ መገኘታቸዉ ተገልጿል፡፡

ይህ ኃይል ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር የጠበቀ ውህደት ለመፍጠር ከወሰዷቸው ተከታታይ እርምጃዎች መካከል የቅርብ ጊዜው ነው።

ሦስቱም አገራት በወታደራዊ መንግስታት (ጁንታዎች) የሚመሩ ሲሆን፤በእስላማዊ አማፂያን ጥቃት እየተፈተኑ ይገኛሉ።

ባለፈው ጥር ወር ላይ የኒጀር መከላከያ ሚኒስትር 5 ሺህ አባላት ያሉት ይህ ኃይል በቀጣናው ያሉ የደህንነት ስጋቶችን ለመቋቋም ‹‹በጋራ ጣልቃ እንደሚገባ››ተናግረው ነበር።

የቡርኪና ፋሶው ጄኔራል ዳውዳ ትራኦሬ የኃይሉ አዛዥ ሆነው የተሾሙ ሲሆን፤ የኃይሉ ዋና የዕዝ ማዕከል በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሜ ላይ እንደሚሆን ታውቋል።

በባማኮ በተካሄደው ስነ-ስርዓት ላይ የሳህል ጥምረት አባል አገራት መከላከያ ሚኒስትሮች፣ እንዲሁም በማሊ ተቀማጭ የሆኑ አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ቡርኪና ፋሶ፣ ማሊ እና ኒጀር የሳህል ጥምረትን የመሰረቱት ከምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ኢኮዋስ ከወጡ በኋላ ነው።

ጥምረቱ ኢኮዋስን ከመፈንቅለ መንግስት ጋር በተያያዘ ኢ-ሰብአዊ ማዕቀቦችን ጥሏል እንዲሁም የአባል አገራቱን ዜጎች ጥቅም የሚፃረር ስራ ይሰራል ሲል ይከሳል።

እስከዳር ግርማ

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *