የቤልጄም ፍርድ ቤት በፓትሪስ ሉሙምባ ግድያ ዳግም ምርመራውን ከፈተ

የኮንጎዉ የነፃነት ታጋይ ተምሳሌት የፓትሪስ ሉሙምባ ቤተሰቦች ፍትህ ለማግኘት ተስፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

የቤልጄም ፍርድ ቤት በ1961 የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ብቸኛው በህይወት ያለ ተጠርጣሪ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ መሆኑን አስታዉቋል፡፡

የሉሙምባ ዘመዶች በግድያው ላይ የቤልጄም ባለስልጣናት ረጅም ጊዜ የዘገየ የህግ ተጠያቂነት እንዲኖር ስለነበራቸው ተባባሪነት ላለፉት 15 ዓመታት ሲወተውቱ ቆይተዋል።

የሟቹ የኮንጎ ጠቅላይ ሚኒስትር የልጅ ልጅ የማ ሉሙምባ በብራስልስ ፍርድ ቤት በዝግ ከሚካሄደው ችሎት በፊት ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል‹‹ጊዜን ወደ ኋላ መመለስ አንችልም፤ነገር ግን የቤልጄም የፍትህ ስርዓት ስራውን እንዲሰራና እውነታውን ይፋ እንደሚያደርግ ተስፋ እናደርጋለን››ብለዋል።

ሉሙምባ በቀድሞዋ ቅኝ ገዢ ቤልጄም ቅጥረኛ ወታደሮች እርዳታ ተረሽኖና አስከሬኑ በአሲድ እንዲሟሟ ከተደረገ ከ65 ዓመታት በኋላ፤ ለፍርድ የሚቀርብ አንድ የቀድሞ ባለስልጣን ብቻ በህይወት ይገኛል።

እርሳቸውም የ93 ዓመቱ ኤቲየን ዳቪኞን ሲሆኑ፤ አንድ ወቅት የአውሮፓ ኮሚሽነር የነበሩና ሉሙምባ በተገደለበት ወቅት ጀማሪ የቤልጄም ዲፕሎማት ነበሩ።

ግለሰቡ በቤልጄም ፌዴራል አቃቤ ህግ በሉሙምባ ህገ-ወጥ እስራትና ዝውውር እንዲሁም አዋራጅና ዝቅ የሚያደርግ አያያዝ በመፈጸም ተሳትፎ ነበራቸው በሚል ተከስሰዋል።

ዳቪኞን የቤልጄም ባለስልጣናት በግድያው ውስጥ ተሳትፎ እንደሌላቸው ሁልጊዜም የሚክዱ ሲሆን፤ ጠበቃቸውም ከዝግ ችሎቱ በፊት ለኤኤፍፒ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

እስከዳር ግርማ

ጥር 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *