1 ሺህ 7መቶ ያህል ሰዎች ለአይን ብሌን ልገሳ ቃል መግባታቸዉ ተገለፀ

ባለፉት ስድስት ወራት 1 ሺህ 7መቶ ሰዎች አይናቸው ለመለገስ ቃል መግባታቸውን የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አስታዉቋል፡፡

ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት ሙሉ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከእጥፍ በላይ እድገት ማሳየት መቻሉን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ታዬ ለኢትዮ ኤፍኤም ተናግረዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት 2 መቶ 47 የአይን ብሌኖችን ከሟች አካል ላይ መሰብሰብ የተቻለ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ይህ አፈጻጸም ካለፈው ዓመት የተሻለ ቢሆንም ከፍላጎቱ አንጻር አሁንም ሰፊ ክፍተት መኖሩ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ህብረተሰቡ ስለ አይን ብሌን ልገሳ ያለው ግንዛቤ እየጨመረ መምጣቱንም አገልግሎቱ አስታዉቋል፡፡

አቶ ሀብታሙ አያይዘውም ህብረተሰቡ በህይወት እያለ ቃል በመግባትና ቤተሰብም ሲያርፍ ፈቃደኛ በመሆን ለወገን ብርሃን እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 13/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *