በውድድሩም የሁለት ጊዜ አሸናፊዋና የቦታው ሪከርድ ባለቤት ኢትዮጵያዊቷ ወርቅነሽ ኢዴሳ (ፎቶ) ለአሸናፊነቱ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷል፡፡
ወርቅነሽ በ2024 ይሄንን የቶኪዮ ማራቶን ስታሸንፍ የገባችበት ሰዓት 2፡18.51 ቀደም ሲል ተይዞ የነበረውን ምርጥ ሰዓት ከሁለት ደቂቃ በላይ በማሻሻል አዲስ የቦታው ሪከርድና የግል ምርጥ ሰዓቷም ሆኖ ተመዝግቦላታል፡፡
ባለፈው ዓመት (2025) በተመሳሳይ 2፡21.00 በሆነ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፈች ሲሆን ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ትጠበቃለች፡፡
አትሌቷ ባለፈው ሚያዚያ ወር በተካሄደው የሀምቡርግ ማራቶን የግል ምርጥ ሰዓቷን ጭምር በማሻሻል 2፡17.55 በሆነ ጊዜ አሸንፋለች፡፡
ወደ አውስትራሊያ በመጓዝም በሲድኒ ማራቶን 3ኛ መውጣቷ የሚታወስ ነው፡፡
በውድድሩ ላይ ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት በዳቱ ሂርጳም ትጠበቃለች፡፡ አትሌቷ ከዓመት በፊት የዱባይ ማራቶንን ስታሸንፍ የገባችበት 2፡18.27 በርቀቱ የግል ምርጥ ሰዓቷ ነው፡፡ በፓሪስ ማራቶንም 2፡20.45 በሆነ ሰዓት ማሸነፏ የሚታወስ ነው፡፡
ኡጋንዳዊቷ ስቴላ ቼሳንግ፣ ጃፓናውያኑ ሚዙኪ ማሱዳ፣ ማኦ ኡሱጊ፣ ሚዙኪ ኒሺሙራ እና ቺቻሩ ሱዚኪም ለኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ጠንካራ ተፎካካሪዎች ይሆናሉ ከሚጠበቁት መካከል ናቸው፡፡
መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን!!
ምስጋናው ታደሰ
ጥር 16/2018 ዓ.ም
