ካለፈው በጀት አመት ጋር ሲነፃፀር ወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ የ1መቶ60 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገለፀ

ካለፈው የ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የጋብቻ ምዝገባ የ10 በመቶ ቅናሽ ቢያሳይም፥ወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ ግን የ1መቶ60 በመቶ ያልተጠበቀ ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል።

በተጠናቀቀው የሪፖርት ጊዜ ውስጥ በከተማው በአጠቃላይ 19 ሺህ 8መቶ የጋብቻ ምዝገባዎች መከናወናቸውን የኩነት ምዝገባ መረጃዎች አመልክተዋል።

ከጠቅላላው የጋብቻ ምዝገባ ውስጥ 5 ሺህ 4መቶ44 የሚሆኑት ኩነቱ በተከሰተበት ወቅት የተከናወኑ ሲሆኑ፤ 1 ሺህ 7መቶ38 የሚሆኑት ደግሞ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ምዝገባ የፈጸሙ ናቸው።

ከፍተኛው ቁጥር የተመዘገበው የጊዜ ገደባቸው ባለፈባቸው ኩነቶች ላይ ሲሆን፥12 ሺህ 6መቶ18 ጋብቻዎች በዚህ መልኩ ተመዝግበዋል።

ከዚህ በተጨማሪም በሸሪዓ ፍርድ ቤት ቅርንጫፎች በኩል 6መቶ55 ወቅታዊ የጋብቻ ምዝገባዎች መከናወናቸው ተገልጿል።

በታዩት ቁጥራዊ መረጃዎች  ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ዕቅድ 90 በመቶ የተሳካ ሲሆን፥በዘገየ የኩነት ምዝገባ ደግሞ 78 በመቶ አፈፃፀም ተመዝግቧል። 

ይሁን እንጂ የጊዜ ገደባቸው ባለፈባቸው ምዝገባዎች ላይ የዕቅዱን 1መቶ36 በመቶ በማሳካት ከፍተኛ አፈፃፀም ማሳየት ተችሏል ነው የተባለው።

የአሁኑ ሪፖርት ካለፈው የ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ሲነፃፀር የጋብቻ ምዝገባ የ10 በመቶ ቅናሽ ቢያሳይም፥ወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ ግን የ1መቶ60 በመቶ ያልተጠበቀ ጭማሪ ማሳየቱ ተመላክቷል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 16/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *