የሀገር ውስጥ ምርቶችን ያበረታታል የተባለ አውደ ርዕይ ተከፈተ

6ኛው ፊንቴክስ የቤት ዕቃዎች፣ ቤተ-ውበትና የግንባታ አጨራረስ አውደ ርዕይ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡

በመድረኩ ላይ እንደተነገረው እ.ኤ.አ በ2024 የዓለም የፈርኒቸር ንግድ እንቅስቃሴ 200 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፤ አፍሪካ በዚሁ ዓመት 45 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ የፈርኒቸር ምርት ከውጭ አስገብታለች።

በ2030 የአፍሪካ ከተሜነት ዕድገት 600 ሚሊዮን ይደርሳል ተብሎ በመገመቱ፣ ለዘርፉ ምርቶች ያለው ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚጨምር ጥናቶች ያመለክታሉ ተብሏል።

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተኪ ምርቶች ተወዳዳሪነት መሪ ሥራ አስፈጻሚ መሳይ ውብሸት “መንግሥት የገቢ ምርቶችን እና ወጪ ምርቶችን ለማመጣጠን በትኩረት እየሠራ ነው” ሲሉ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተናግረዋል፡፡

ከጥር 19 እስከ ጥር 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሚካሄደው አውደ ርዕይ፤ ከ50 በላይ የሀገር ውስጥ ኩባንያዎች እና ከ4ሺህ በላይ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

አውደ ርዕዩ አምራቾች እና አስመጪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ የሚያስተዋውቁበት መድረክ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 19/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *