በአመቱ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ የጤና ተቋማት መድኃኒት ይገዛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህን ያለዉ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ነዉ።
ተቋሙ መድኃኒት ጨምሮ የህክምና መሣሪያዎችን ተቋሙ በራሱ እንዲሁም ከጤና ሚኒስቴር የሚቀርብ መሆኑን ተናግሯል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልገሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ በባለፉት ስድስት ወራት የመድኃኒት አቅርቦት ለጤና ተቋማት ተደራሽ በማድረግ የአቅርቦት ደረጃዉ 72 በመቶ ሆኖ መታየቱን ተናግረዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ለመድሀኒት ዉል በተገባለት የአቅርቦት ስርአት መሠረት ከ5 ሺህ 2 ተቋማት ጋር ዉል በመግባት መድኃኒት እያቀረበ መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ በዋጋ ደረጃ ወደ 8 ቢሊዮን ብር የሚሆን የመድኃኒት ግዥ የጤና ተቋማት ከአቅራቢ ድርጅቱ ግዥ ፈፅመዋል ሲሉም ገልፀዋል።
በአመቱ ከ20 ቢሊየን ብር በላይ የጤና ተቋማት መድኃኒት ይገዛሉ ተብሎ ይጠበቃል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በዉሉ መሠረት መድኃኒት ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ ነዉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የጤና ተቋማት የገጠማቸው የህክምና መሣሪያዎች እጥረት ለሟሟላት እንዲቻል በዘንድሮው አመት 2 መቶ 90 የሚሆን የደም መመርመሪያ መሣሪያን ማሽን በተመጣጣኝ ዋጋ ለጤና ተቋማት ማቅረቡን ገልፆል።
አገልግሎት በዛሬው እለት በዋና መስሪያ ቤቱ “CBC” የተሰኙ 80 ያህል የላብራቶሪ መመርመሪያ መሣሪያዎችን ለክልል የጤና ቢሮዎች በነፃ አስረክቧል።
ከሆስፒታሎች ይልቅ እነዚህን መሣሪያዎች በጤና ተቋማት ተደራሽ ለማድረግ የታለመ መሆኑን በርክክብ መድረኩ ሰምተናል።
አገልግሎቱ ከጤና ሚኒስቴር ጋር አደረጉት ባለዉ የዳሰሳ ጥናት የጤና ተቋማት የላብራቶሪ መመርመሪያ እጥረት የማህበረሰብ የቅሬታ ምንጭ ሆኖ ማስተዋሉን ተናግሯል።
በዛሬዉ የርክክብ ስርአት ላይ የሶማሌ÷ የሲዳማ÷ የማእከላዊ ኢትዮጵያ እና የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ሌሎች የክልል ቢሮ ተወካዮች በተገኙበት ተደርጓል።
ቁምነገር አየለ
ጥር 19/2018 ዓ.ም
