የቻይና ብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ፥ የሀገሪቱ አማካይ ዓመታዊ የሙቀት መጠን ለሁለት ተከታታይ ዓመታት 10.9 ዲግሪ ሴልሺየስ በመሆን በክብረ ወሰን መመዝገቡን አስታውቋል።
ይህም በታሪክ ከፍተኛው የሙቀት ቀናት የተመዘገቡበት ዓመት ያደርገዋል።
አስተዳደሩ ይህንን ያስታወቀው የ2025 የዓለም የአየር ንብረት መረጃን ይፋ ባደረገበት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት በጥር ወር ባወጣው መረጃ መሰረት፥ 2025 በዓለማችን በሙቀት መጠን ከፍተኛ ከተባሉ ሦስት ዓመታት ውስጥ አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።
እንደ አስተዳደሩ ገለጻ የቻይና ዓመታዊ አማካይ የሙቀት መጠን ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፥ 2025 ሀገሪቱ ብሔራዊ መዝገብ መያዝ ከጀመረችበት ከ1961 ወዲህ በጣም ሞቃታማው ዓመት ሆኖ ተመዝግቧል።
ከባድ ዝናብ እና ከፍተኛ ሙቀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸው እንደ ጎርፍ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ያሉ ስጋቶችን አባብሰዋል።
ከሰኔ መጨረሻ እስከ መስከረም መጀመሪያ ድረስ በማዕከላዊ እና በምስራቅ ቻይና ቀጣይነት ያለው ከፍተኛ ሙቀት የታየ ሲሆን፥ አማካይ የዝናብ መጠንም ከተለመደው በ4.5 በመቶ ከፍ ብሎ ተመዝግቧል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
ጥር 21/2018 ዓ.ም
