አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አርማ እና መለያ ቀለም በመቀየር፣ ዘመናዊነትን የተላበሰ አዲስ የብራንድ መለያ መተግበሩን በይፋ አስታወቀ።
ባንኩ ይህን ለውጥ ያበሰረው “ምን እንደማስብ ታውቃላችሁ?” በሚል በሰፊው በተሰራጨና የደንበኞችን ትኩረት በሳበ የማስታወቂያ ዘመቻ ታጅቦ ነው።
የባንኩ አመራሮች እንደገለጹት፣ ይህ የብራንድ ለውጥ የምስልና የቀለም ሽግግር ብቻ ሳይሆን፣ ተቋሙ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት በማዘመንና የቴክኖሎጂ አቅሙን በማሳደግም ነው ብለዋል።
ባንኩ ይበልጥ ቀለል ወዳለና ለዲጂታል ባንኪንግ ምቹ ወደሆነ አርማ የተሸጋገረው፣ በኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን ተወዳዳሪነት ለማጎልበት መሆኑ ተጠቁሟል።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ በ2016/17 በጀት ዓመት አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠኑን 44 ቢሊዮን ብር ማድረሱ ይታወሳል፡፡
ሐመረ ፍሬው
ጥር 22/2018 ዓ.ም
