ዩጋንዳ የውጭ በጀት ድጋፍን በ84 በመቶ ለመቀነስ ማቀዷን ገለጸች

ዩጋንዳ ከሚቀጥለው ሐምሌ ወር ከሚጀምረው የፋይናንስ ዓመት አንስቶ፤ የውጭ አገር የበጀት ድጋፍን በየዓመቱ በ84 በመቶ ለመቀነስ ማቀዷን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ፤ አብዛኛውን ጊዜ በብድር እና በእርዳታ መልክ የሚገኘው ይህ ድጋፍ ከ5መቶ86 ሚሊየን ዶላር ወደ 92.72 ሚሊየን ዶላር ዝቅ ይላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጿል።

ሚኒስቴሩ ለዚህ ከፍተኛ ቅናሽ ዝርዝር ምክንያት ባይሰጥም መንግስት የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብን ለማጠናከር ስልቶችን በመተግበር ላይ ትኩረት አድርጓል ነዉ ያለዉ፡፡

የዩጋንዳ ኢኮኖሚ በማገገም ላይ ሲሆን፤በ2026/27 የፋይናንስ ዓመት ገቢው በ9 በመቶ ያድጋል ተብሎ ትንበያ ተደርጓል፡፡

ሀገሪቱ በዚህ ዓመት የድፍድፍ ነዳጅ ምርት ለመጀመር ተስፋ የምታደርግ ሲሆን፤ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለፈው ዓመት እንደተነበየው ከነዳጅ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ የሀገሪቱን የኢኮኖሚ ዕድገት መጠን ወደ ባለ ሁለት አሃዝ ሊያሳድገው ይችላል።

በተጨማሪም መንግስት እየናረ የመጣውን የሕዝብ ዕዳ ለመቀነስ እንዲረዳው፤በሚቀጥለው የፋይናንስ ዓመት የሀገር ውስጥ ብድር አሰባሰብን ካለፈው ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ21.1 በመቶ ለመቀነስ አቅዷል ሲል አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።

እስከዳር ግርማ

ጥር 22/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *