በአዲስ አበባ የትራፊክ አደጋ ከተፈጥሮ ሞት ቀጥሎ ሁለተኛው የሞት መንስኤ እየሆነ መምጣቱ ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ አደጋ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱንና በከተማዋ ከሚከሰቱ ሞቶች ከተፈጥሮ ሞት ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጡን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ለአደጋው መጨመር መሰረታዊ ምክንያቱ የአሽከርካሪዎችና የእግረኞች የደንብ መተላለፍ መሆኑን የገለጹት የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፥በተለይም አሽከርካሪዎች የሚያደርጉት የፍጥነት ወሰን መጣስ ለአደጋው መባባስ ዋናው ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን የከተማዋ የመንገድ መሰረተ ልማት እየዘመነ ቢመጣም፥ የአሽከርካሪውና የመንገድ ተጠቃሚው ባህል ከዘመናዊነቱ ጋር ተጣጥሞ መሄድ አለመቻሉ አደጋውን ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት ፈተና ውስጥ እንደከተተው አብራርተዋል።

ህብረተሰቡ፣ ወላጆች እና መገናኛ ብዙሃን በዚህ ጉዳይ ላይ አበክረው ሊሰሩ እንደሚገባና ካለው ዘመናዊነት ጋር የሚሄድ የመንገድ አጠቃቀም ባህል ሊዳብር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ጥር 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *