የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ከ74 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ

አገልግሎቱ በበጀቱ ግማሽ ዓመት 74.43 ቢሊየን ብር ገቢ አግኝቻለሁ ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢ/ር አብዱልበር ሸምሱ፤ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ቀርበዉ የተቋማቸዉን የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ለቋሚ ኮሚቴው ባቀረቡት ሪፖርት፤ በግማሽ ዓመቱ 65.5 ቢሊየን ብር ለማግኘት ታቅዶ 74.43 ቢሊየን ብር መገኘቱን ገልጸዋል፡፡

ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ59 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን ነዉ የተናገሩት፡፡

በጅቡቲ ወደብ በኩል ወደ ሀገር ውስጥ ከገባው 4.7 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ የደረቅ ጭነት ውስጥ ድርጅቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ድርሻ በመሸፈን ማጓጓዙን አንስተዋል፡፡

በተለይም የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ ሥራ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ1መቶ91 በመቶ ዕድገት ማሳየቱን በዝርዝር አብራርተዋል።

በሪፖርቱም የውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ የሎጅስቲክስ አገልግሎት ውጤታማነትና የማሪታይም ሥልጠና አፈጻጸም ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችን በዝርዝር አቅርበዋል።

ሀና ሰይፉ

ጥር 27/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *