የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አመታዊ የቴሌቪዥን ግብርን መቀበል ሊያቆም እንደሚችል ፍንጭ መስጠቱ ይታወሳል።
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 1278/2015 ዓ.ም በተሰጠው ስልጣን መሰረት አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ክፍያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፍጆታ ሂሳብ ክፍያ ቢል ጋር እንዲሰበስብ መወሰኑ የሚታወቅ ነዉ።
ሆኖም አመታዊ የቴሌቪዥን አገልግሎት ግብርን ቤት ለቤት እየተጠየቅን ነዉ በሚል ከደንበኞች ቅሬታ መነሳቱ የሚታወስ ነዉ።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በዛሬዉ እለት የ 2018 በጀት አመት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀሙን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥቷል።
የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጠተዋል።
ኢ/ር ጌቱ ጉዳዩ ዙሪያ ከኢትዩጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስፈፃሚ ጋር እንደተነጋገሩበት ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ችግሩን እንደሚፈታዉ እና አመታዊ የቴሌቪዥን ግብርን ደግመዉ እንደማይጠይቁ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደነገሯቸዉ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ተናግረዋል።
አገልግሎቱ ጉዳዩ እንዲፈታ ዝም አለማለቱን እና የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አመታዊ የቴሌቪዥን ግብርን መሰብሰብ እንዲያቆም መነጋገራቸዉን ሰምተናል።
ከንግግሩ በኋላ ጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን አልሰማንም ካሉም ግን ሁለቱ ተቋማት በጋራ ሆኖ መፍታት እንደሚችሉ ማሳወቅ እንደሚፈልጉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ ገልፀዋል።
ከዚህ ቀደም አገልግሎቱ የግብር አሰባሰቡ ዙሪያ የኢትዩጵያ ቴሌቪዥን አሰራሩን እንዲያርም እንደሚነጋገር ካልሆነ ግን ደንበኞችን ማስቀየም ስለማያስፈልግ ዉሉን ወደ ማቋረጥ እንደሚሄዱ አገልግሎቱ ስራ አስፈፃሚ ኢ/ር ጌቱ ገረመዉ አስታውቀዉ ነበር።
ቁምነገር አየለ
ጥር 28/2018 ዓ.ም
