የማሊ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሳ ማራን የእስራት ቅጣት አጸና

የማሊ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ለፖለቲካ እስረኞች ድጋፋቸውን የሚገልጽ መልዕክት በማህበራዊ ሚዲያ በማጋራታቸው ጥፋተኛ የተባሉትን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙሳ ማራን የእስራት ቅጣት አጽንቷል።

ከፈረንጆቹ 2014 እስከ 2015 ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉት ማራ፤ ባለፈው ጥቅምት ወር የመንግስትን ተዓማኒነት በማጉደፍ እና ህጋዊ ስልጣንን በመቃወም ወንጀል ተከሰው ነበር።

በዋና ከተማዋ ባማኮ የሚገኙ አንድ ዳኛ የቅጣት ውሳኔያቸውን አረጋግጠዋል፤ ውሳኔውም የሁለት ዓመት እስራት አንዱ ዓመት በገደብ የታገደ ሲሆን እንዲሁም የ5መቶ ሺህ ፍራንክ የገንዘብ ቅጣት ነው።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጠበቃ የህግ ትግሉ ገና አለመጠናቀቁን በመግለጽ፤ ጉዳዩን ለማሊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ እንደሚሉ ገልጸዋል፡፡

ማሊ በ2020 እና 2021 ከተካሄዱት የመንግስት ግልበጣዎች በኋላ በወታደራዊ ጁንታ እየተመራች ትገኛለች።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ባለስልጣናቱ በፖለቲከኞች፣ በመገናኛ ብዙሃን እና በፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ያነጣጠረ የተቃውሞ ድምጾችን የማፈን እርምጃቸውን አጠናክረዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

እስከዳር ግርማ

የካቲት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *