የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ከ8 ሺህ 700 ለሚሆኑ አባወራዎች የምግብ ድጋፍ ተደረገ

ዛሬ በተደረገው የፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ ከኪንግ ሰልማን የሰብአዊ እርዳታ እና የመርጃ ማእከል በተገኘ ድጋፍ ለችግረኛ አባወራዎች የዘይትና ዱቄት ድጋፍ የመስጠት መርሀገብርም ተካሄዷል።

ይህ የድጋፍ ፕሮጀክት በየአመቱ እንደሚካሄድና በቦረና ፣ በወሊሶና በሶማሌ ክልልም እንደሚካሄድ የአክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ ሳሊሁ ሱልጣን ቢሎ ገልጸዋል።

አቶ ሳሊሁ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ ለ5ተኛ ጊዜ የሚካሄድና 40 ሺህ የሚደርሱ ችግረኞችን ለማዳረስ ያለመ ነው ብለዋል።

አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ አሁንም ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ስደተኞችን፣ ተፈናቃዮችን እና ሌሎች በጣም ተጋላጭ የሆኑ ማህበረሰቦችን እያገለገለ መሆኑን አቶ ሳሊሁ ሱልጣን ቢሎ ገልጸዋል።

ድርጅቱ አሁን ላይም ከተለያዩ የመንግስት ባለድርሻ አካላት ጋር ከ UN ኤጀንሲዎች፥ ከአለም አቀፍ እና ሀገር በቀል ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር በትብብር ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።

በኢትዮጵያ ውስጥ እና በIGAD አባል ሀገራት ውሰጥ እያከናወነ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።

አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢትዮጵያ (ANE) ላለፉት 13 ዓመታት ስደተኞችን፤ ተፈናቃዮችን እና በተለያየ ምክንያት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ይገኛል።

ድርጅቱ በምግብና በውሃ፣ በመጠለያ እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ድጋፍ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ልማት እና በሌሎችም ተቀራራቢ ዘርፎች ድጋፍ አድርጓል።

አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ በሀገራችን የተለያዩ ክልሎቹ በለደተኞች ጉዳይ ላይ የሚሰራና እንዲሁም በርካታ የሰብዓዊና የልማት ሥራዎችን በማከናወን ይገኛል።

ድርጅቱ ከሲቪል ማሀበረሰብ ኤጀንሲ በቁጥር 2825 በኢትዮጵያ ነዋሪዋች የበጎ አድራጎት ስም የተመዘገበ ተቋም ነው፡፡

የውልሰው ገዝሙ

የካቲት 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *