የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ከ10 አመት በኋላ ነው ።
ይህ ጉብኝት በሁለቱ ሀገራት መካከል በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ የተከፈተበትን 100ኛ ዓመት የሚዘከርበት በመሆኑ ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እስከ 16ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ወደ ኋላ የሚዘልቅ ታሪክ ያለው ነው።
የሁለቱን ሀገራት የቆየ ግንኙነት እያደገ የመጣውን የኢኮኖሚ ትስስር እና የአንካራን ቀጣናዊ ዲፕሎማሲያዊ ሚና አጉልቶ ያሳያል።
በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግብዣ መሰረት ለዛሬ ማክሰኞ የታቀደው ይህ ጉዞ፤ ፕሬዝዳንት ኤርዶዋን ከአስር አመታት በላይ በሆነ ጊዜ ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት የመጀመሪያው ጉብኝት ነው።
በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ቤርክ ባራን እንደገለጹት፤ ይህ ጉብኝት ቀድሞውኑ ጠንካራ የሆነውን ግንኙነት ከፍታ የሚያሳይ ነው ፤ ቱርክ እና ኢትዮጵያ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፎች ስልታዊ ግንኙነት አላቸው ሲሉ ገልጸዋል።
ጉብኝቱን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑም ተገልጿል ሲል የዘገበው ቲአርቲ ዎርልድ ኒውስ ነው፡፡
ሀና ሰይፉ
የካቲት 10/2018 ዓ.ም
