‹‹ስራ በዝቶብኛል››በሚል ሰበብ ህፃናትን ሆድ የሚያለሰልስ መድኃኒት ስታበላ የነበረች መምህርት በቁጥጥር ስር ዋለች፡፡

በአሜሪካ ኢሊኖይ ግዛት የምትገኝ የ23 ዓመቷ የመዋለ ህፃናት መምህርት ይዘል ጄ. ጄ፤ስራዋን ለማቅለልና ህፃናቱን ወደ ቤታቸው እንዲሄዱ ሰበብ ለመፍጠር ሆድ የሚያለሰልስ መድኃኒት (Laxative) ስታበላቸው ተገኝታ በቁጥጥር ስር ውላለች።

መዋዕለ ህፃናቱ ‹‹የታመሙ ህፃናት ወደ ቤታቸው ተመልሰው ለ24 ሰዓት መቆየት አለባቸው›› የሚል ደንብ ያለው ሲሆን፤ መምህርቷም ይህንን አጋጣሚ ለመጠቀም ዕድሜያቸው ሁለት ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ህፃናትን መድኃኒቱን ‹‹ከረሜላ ነው››በማለት ታታልላቸው ነበር ተብሏል፡፡

ድርጊቱ የታወቀው በርካታ ወላጆች ልጆቻቸው ላይ የተከሰተውን ድንገተኛ የተቅማጥ በሽታ ተከትሎ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠታቸው ሲሆን፤መምህርቷም ድርጊቱን መፈጸሟን ለፖሊስ አምናለች።

አንድ እናት እንደገለጹት ልጃቸው ለሳምንታት በሆድ ህመም ሲሰቃይ ቢቆይም ሐኪሞች ምክንያቱን ሊደርሱበት አልቻሉም ነበር፤ አሁን ግን ህፃኑ ከመድኃኒቱ መቋረጥ ጋር ተያይዞ በከፍተኛ የሆድ ድርቀት እየተሰቃየ ይገኛል።

መምህርቷ በህፃናት ጤና ላይ አደጋ በመጣል እና በከባድ ጥቃት ሙከራ ወንጀል ተከሳ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ተሰጥቷታል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡

ሐመረ ፍሬው

የካቲት 10/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *