አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር ለ19 አባላቱ ተሽከርካሪዎችን አስረከበ

አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ስራ ማህበር የአባላቱን የኢኮኖሚ አቅም ለማጠናከርና የስራ እድል ለመፍጠር የጀመረው ጥረት አካል የሆነውን የተሽከርካሪ ርክክብ በዛሬው እለት አከናውኗል።

ማህበሩ በዛሬው እለት በየካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው መርሃ-ግብር ለ19 አባላቱ የመኪና ቁልፍ አስረክቧል።

በአሚጎስ የአዲስአበባ ዲስትሪክት ዋና ዳይሬክተር አቶ ገለታው ፀጋው በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፤ ይህ መርሃ-ግብር አባላት በትራንስፖርት ዘርፍ ተሰማርተው ቋሚ ገቢ እንዲያገኙና ራሳቸውን እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

አሚጎስ በአሁኑ ወቅት ከ14 ሺህ በላይ አባላት ያሉት ሲሆን፣ ከ6 ቢሊዮን ብር በላይ ሀብት ማፍራት እንደቻለም ተገልጿል።

ማህበሩ እስካሁን ከ6 ሺህ ለሚበልጡ አባላቱ ከ7 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር የሰጠ ሲሆን፣ በተለይም ለመኪና ብድር 3.33 ቢሊዮን ብር በማቅረብ አባላቱ የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ እያገዘ ይገኛል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች 22 ቅርንጫፎችን የከፈተ ሲሆን፣ በቅርቡም በሀዋሳና በጅማ ቅርንጫፎችን በመክፈት ተደራሽነቱን ለማስፋት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

ልዑል ወልዴ

የካቲት 12/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *