የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀልን ለመከላከል ባለፉት ዓመታት የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ጨምሮ ዘመናዊ አሰራሮችን እየተገበረ ቢሆንም፥ያለ ህብረተሰቡ ተሳትፎ ውጤታማ መሆን እንደማይችል የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፥ ተናግረዋል።
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና ብዛት ያለው የሰው ኃይል ቢኖረውም በእያንዳንዱ ቤት ደጃፍ፣ በየውስጥ ለውስጥ መንገዱና መተላለፊያው ላይ በአካል ተገኝቶ መጠበቅ ስለማይችል የህብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አስታውቋል።
ነዋሪዎች አካባቢያቸውን በመጠበቅና አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ለፖሊስ በመጠቆም ተባባሪ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርቧል።
ወላጆች ለልጆቻቸው ስለ ወንጀልና ስለ ትራፊክ አደጋ አስከፊነት ከልጅነታቸው ጀምሮ በማስተማር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 12/2018 ዓ.ም
