የሰሜን ኮሪያ ገዥ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ-ጆንግን ወደ ከፍተኛ የሥልጣን እርከን እንዳደጉ የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል፡፡
ይህም በሀገሪቱ ውስጥ ያላትን ሰፊ ተፅዕኖ የሚያሳይ ነው ተብሏል።
የወንድማቸው የቅርብ ረዳት እንደሆኑ የሚታሰቡት ኪም ዮ-ጆንግ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ የዲፓርትመንት ዳይሬክተር ሆነው መሾማቸውን የኮሪያ ማዕከላዊ ዜና ወኪል ዘግቧል።
እስካሁን የትኛውን ክፍል እንደሚመሩ በግልጽ ባይታወቅም፤ ቀደም ሲል በፓርቲው የፕሮፓጋንዳ ክፍል ውስጥ ከፍተኛ የሥልጣን ቦታ ነበራቸው።
ባለፉት ዓመታት ኪም ዮ-ጆንግ በዲፕሎማሲ፣ በኒውክሌር ድርድር እና በሌሎች የመንግሥት ጉዳዮች ላይ ጎልቶ የሚታይ ሚና በመጫወት በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ካሉ እጅግ ተደማጭነት ያላቸው ግለሰቦች አንዷ ሆነው ብቅ ብለዋል።
‹‹ኪም ዮ-ጆንግ፣ ኪም ጆንግ ኡን ሊያምኗቸውና ሊደገፏቸው ከሚችሉ ጥቂት ሰዎች መካከል አንዷ ናቸው›› ሲሉ የቀድሞ የሰሜን ኮሪያ ተወላጅ ተመራማሪ አህን ቻን-ኢል ተናግረዋል።
‹‹በሲንጋፖር እና በሃኖይ ከትራምፕ ጋር ለተደረጉት ስብሰባዎችም እንደ ከፍተኛ የሥራ መኮንን አገልግለዋል። ልምድ ያካበቱና የበሰሉ ናቸውም››ብለዋል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
