ትናንት በሙርታላ ሙሐመድ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተነሳ የእሳት አደጋ ምክንያት በረራ ለጊዜው ተቋርጦ ነበር።
የናይጄሪያ ባለሥልጣናት ባወጡት መግለጫ ስድስት ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን፤ ሁሉም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
በአደጋ ጊዜ ደራሽ ቡድኖች ከመታደጋቸው በፊት አሥራ አራት ሰዎች በበረራ መቆጣጠሪያ ማማ ውስጥ ተዘግቶባቸው ቆይተዋል።
የእሳት አደጋው ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ በተርሚናል 1 አንደኛ ፎቅ ላይ በሚገኝ የሰርቨር ክፍል ውስጥ እንደተነሳ ታውቋል።
ቃጠሎው በ5መቶ ሚሊየን ዶላር ወጪ እድሳት እየተደረገለት ያለውን የአውሮፕላን ማረፊያውን የመነሻ አዳራሽ ጎድቶታል ነዉ የተባለዉ።
የናይጄሪያ የአየር ክልል አስተዳደር ኤጀንሲ፤ አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ ጊዜያዊ የቁጥጥር ማማ ለማቋቋም እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
የበረራ አገልግሎቱ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ላይ ተጀምሯል ሲል አፍሪካ ኒዉስ ዘግቧል።
ሊዲያ ደሳለኝ
የካቲት 17/2018 ዓ.ም
