በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 2 ሺህ 9 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸዉን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡
ባለፈው ሳምንት ውስጥ በተደረገ 8 ዙር በረራ የተመለሱት ሁሉም ወንዶች ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 38 ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5/2018 የተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 56 ሺህ 2መቶ25 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
የካቲት 24/2018 ዓ.ም
