ይህ የተባለዉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረውን አለምአቀፉን የሴቶች ቀንን አስመልክቶ በዛሬዉ ዕለት በሰጠዉ ጋዜጣዊ መገለጫ ላይ ነዉ።
መግለጫው የሰጡት የሚኒስቴሩ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ፥ የቀኑን አከባበር አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ በኢትዮጵያ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረዉ አለምአቀፉ የሴቶች ቀን በተለያዩ ንቅናቄ ተከብሮ የሚያልፍ መሆኑን ተናግረዋል።
ሚኒስቴሯ የሴቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚ ዙሪያ በገጠሪቷ ኢትዮጵያ የሴቶችን የመሬት ባለቤትነት 28 ከመቶ በላይ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
ከዚህም ጋር ተያይዞ 60 በመቶ ያህል የመሬት ባለቤትነት ማረጋገጫ እንዲኖራቸዉ ተደርጓል ተብሏል።
አያይዘዉም የፖለቲካ ተሳትፎን በተመለከተ እንደራሴዎቹ ምክር ቤት የሴቶች የዉክልና ድርሻ 41 በመቶ ደርሷል ሲሉ ሚኒስቴሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ለ50ኛ ጊዜ የሚከበረዉ አለምአቀፉ የሴቶች ቀን ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር የዉይይት መድረኮች እንደሚደረጉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ከ1950ዎቹ ጀምሮ የሴቶች ተሳትፎ በሁሉም ዘርፍ ምን ይመስል ነበር? አሁን ያለበትስ? ደረጃ የሚገመገምበት ይሆናል ሲሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገረዋል።
የሴቶች የመደራጀት እንቅስቃሴ እና የሴቶች የልማት ፓኬጅ ያመጣዉን ለዉጥ የሚገመገምበት መድረክ በዚሁ በአለምአቀፍ የሴቶች ቀን የሚዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል።
ከሴቶች ጥቃት እና ከጥቃቱ በኋላ የማገገሚያ ማዕከላትን እያሰፋን ነዉ ያለዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የህግ አካሄዶችን ተከትሎ የሚሰሩ ሰፊ ስራዎች አሉ ብሏል።
ቁምነገር አየለ
የካቲት 25/2018 ዓ.ም
