ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት የቀድሞው የኢራን የስለላ ኃላፊ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ኢራን የቀድሞውን የእስላማዊ አብዮታዊ ዘበኛ ኃይል (IRGC) የስለላ ኃላፊ ሆሴን ታኢብን፣ ከእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ወንጀል በቁጥጥር ሥር ማዋላቸው ተዘግቧል።

ለከፍተኛው የደኅንነት ባለሥልጣን መታሰር እንደ ምክንያት የተጠቀሰው፤ በቅርቡ አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ከመፈጸማቸው 20 ደቂቃዎች ቀደም ብሎ፣ ሆሴን ታኢብ ከሀገሪቱ ጠቅላይ መሪ አሊ ካሜኒ ጋር የነበራቸውን ስብሰባ “ታምሜአለሁ” በሚል ምክንያት በድንገት አቋርጠው መውጣታቸው ነው።

ይህ ድርጊታቸው ስለ ጥቃቱ አስቀድመው መረጃ እንደነበራቸውና ከጠላቶቻቸው ጋር ሳይተባበሩ እንዳልቀረ ከፍተኛ ጥርጣሬን ፈጥሯል።

ሆሴን ታኢብ ለረጅም ዓመታት የኢራንን የስለላ መዋቅር ሲመሩ የቆዩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሰው ነበሩ ሲል የዘገበው አይሪሽ ታይምስና ኢራን ኢንተርናሽናል ነው፡፡

ልኡል ወልዴ

የካቲት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *