አደጋው የተከሰተው ትናንት ሌሊት በዞኑ ካምባ ዙሪያ፣ ጋጮ ባባ እና ቦንኬ በተባሉ ወረዳዎች በጣለው ዝናብ ነው።
የዞኑ መስተዳድር የመሬት መንሸራተት ሊያጋጥምባቸው በሚችሉ ገደላማና ተዳፋት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ነዋሪዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ቅስቀሳ እያደረገ ነው።
የጋሞዞን ኮሙኒኬሽን ቢሮ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ባወጣው መግለጫ የዞኑ አስተዳደር በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦችና ለመላው የዞኑ ሕዝብ መጽናናት ተመኝቷል።
በዛሬው ዕለትም በዞኑ ከጣለው ከባድ ዝናብ ጋር ተያይዞ በተከሰቱ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች አስቸኳይ ድጋፍ ለማድረግና ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ የሚያስችል ምክክር ማካሄዱን ገልጿል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ዶ/ር ደምሴ አድማሱ «በአደጋው ምክንያት ተፈናቅለው ለችግር የተጋለጡ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የመጠለያ፣ የምግብና የህክምና እርዳታ በልዩ ትኩረትና በአስቸኳይ ሊቀርብ እንደሚገባ ማሳሰባቸውም ተገልጿል።
በጋሞ ዞን በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍና የተደቀነውን ስጋት በጋራ ለመወጣትም የእርዳታ ጥሪም አድርጓል።
በምሥራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሰሞኑን የጎርፍ አደጋዎች እየተከሰቱ ነው።
ባለፈው ዓርብ ዕለት በጎረቤት ኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢና ሌሎች አካባቢዎች የወረደው ኃይለኛ ዝናብ ያስከተለው ጎርፍ ከ40 በላይ ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል።
በንብረት ላይም ከፍተኛ ጉዳት አስከትሏል።
መጋቢት 02/2018 ዓ.ም
