የመምህር ዘላለም ወንድሙን የበጎ አድራጎት ሥራ ለማስቀጠል የገቢ ማሰባሰቢያ ተጀመረ

ዕድሜያቸውን ለወንጌልና ለችግረኞች አገልግሎት የሰጡት የታዋቂው አገልጋይ የመምህር ዘላለም ወንድሙን መልካም አሻራ ለማስቀጠል የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ተከፍቷል።

መምህር ዘላለም በወንጌል ተልዕኮ ወደ ውጭ ሀገር በሄዱበት ወቅት በድንገት በደረሰባቸው ህመም ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይታወሳል።

ቤተሰቦቻቸውና አድናቂዎቻቸው መምህሩ ሲመኙት የነበረውን የበጎ አድራጎት ሥራ ለማስቀጠልና ቋሚ መታሰቢያ ለማቆም ዓለም አቀፍ የ’GoFundMe’ (ጎ ፈንድ ሚ) ገጽ ከፍተዋል።

ይህ የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ መምህሩ ለድሆች የነበራቸውን ልባዊ ፍቅርና ትጋት በቋሚነት ለማስታወስ ያለመ ሲሆን፤ በሀገር ውስጥና በውጭ የምትገኙ በጎ አድራጊዎች በ’GoFundMe’ ድረ-ገጽ ላይ በመግባት ‘መምህር ዘላለም ወንድሙ’ ብለው በመፈለግ የበኩላችሁን አሻራ እንድታሳርፉ ጥሪ ቀርቧል።

የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የአሸኛኘትና የቀብር ሥነ-ሥርዓት በመስቀል አደባባይ ይከናወናል

መምህር ዘለዓለም ወንድሙ የአሸኛኘት መርሐ-ግብር የቤተክርስቲያኒቱን ክብር በሚመጥን መልኩ በመስቀል አደባባይ እንደሚፈጸም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አስታወቀ።

​የመርሐ-ግብሩ ዝርዝር፡

​ረቡዕ መጋቢት 2 ቀን፡ የአስከሬን ጉዞ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ይደረጋል።

​ሐሙስ መጋቢት 3 ቀን፡
​ከጠዋቱ 12፡00፡ አስከሬኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ይደርሳል።

​ከጠዋቱ 1፡00 – 3፡00፡ ከአውሮፕላን ማረፊያ እስከ ቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል በዝማሬና በታላቅ ታጀቦ ጉዞ ይደረጋል።

​ከጠዋቱ 3፡00 – 5፡00፡ ከቦሌ መድኃኔዓለም በመነሳት በመለከትና በነጋሪት ድምፅ ታጅቦ ወደ መስቀል አደባባይ ይጓዛል።

​ከጠዋቱ 5፡00 – 8፡00 (መስቀል አደባባይ)፦ ያሬዳዊ ዝማሬ፣ የሕይወት ታሪክ ንባብ፣ የምስክርነት ቃላት እና የወንጌል ትምህርት በብፁዓን አባቶች ቡራኬ ይከናወናል።
​ከቀኑ 9፡00፡ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሥርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል።

መምህር ዘለዓለም የዕለቱ “ሰማያዊ ሙሽራ” በመሆናቸው፣ ለመሸኘት የሚመጡ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች በሙሉ ነጭ ልብስ ለብሰው እንዲገኙ ጥሪ ቀርቧል።

ጣቢያችን ኢትዮ ኤፍኤም በመምህር ዘላለም ወንድሙ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል ። ለቤተሰቡቻቸው ለወዳጅ ዘመዱቻቸው መፅናናትን ይመኛል።

መጋቢት 02/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *