ለትርፍ ያልተቋቋመ ዓለምዓቀፍ ግብረ ሰናይ ደርጅት እንደሆነ የገለፀው ሪች ፎኤ ቼንጅ፤ በዋናነትም በማህበረሰቡ ዉስጥ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የሚንቀሳቀሱ ሥራ ፈጣሪዎችን አግዛለሁ ብሏል።
በዚህም እስከዛሬ 1 ሺ 9 መቶ ገደማ የሚሆኑ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የሚገኙ የንግድ ሃሳቦችንና ተቋማትን ስንደግፍ ቆይተናል ሲሉ በሪች ፎር ቼንጅ ሲኒየር ፕሮጀክት ማኔጀር ኤልሳቤት ጸጋዬ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ተቋሙ መንግስት ትኩረት ለሰጠው ስራ ፈጠራ እና የማህበረሰብ ችግር ፈቺ ፕሮጀክቶችን እየደገፈ እንደሆነ የገለጹት ሲኒየር ፕሮጀክት ማኔጀሯ ” ፕሮጀክቱን ስናካሂድ እንደ የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት፣ የአዲስ አበባ ጽዳት ማኔጅመንት ኤጀንሲ፣ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ቢሮ፣ እንዲሁም የፌደራል አካባቢ ጥበቃ ባለስጣልን አብረውን በጋራ የሚሰሩ ናቸው“ ብለዋል፡፡
እነዚህ የመንግስት አካላት ለጀማሪ የንግድ ስራ ፈጣሪዎችና ለማህበረሰብ ስራ ፈጣሪዎች የተሻለ የስራ ከባቢ እንዲፈጠርላቸው ፖሊሲሰዎችን በማውጣትና በማስፈጸም የራሳቸውን አስተዋጽዖ እያበረከቱ መሆናቸውንም ኤልሳቤት ጸጋዬ ገልጸዋል፡፡
ሪች ፎር ቼንጅ በተለያዩ ጊዜያት በሚያዘጋጃቸው መድረኮች ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የእርስ በርስ ትውውቅና የገበያ ትስስር እያመቻቸ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
አዲስአለም አበበ
መጋቢት 03/2018 ዓ.ም
