በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1 ሺህ 1መቶ92 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸዉ ተሰምቷል፡፡
በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 5 ዙር በረራ የተመለሱት 1ሺህ 1መቶ73 ወንዶች እና 16 ሴቶች እንዲሁም 3 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 34 ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።
መስከረም 5 ቀን 2018 በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን 59 ሺህ 52 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በህገወጥ የሰዎች ዝውውር አስከፊነት ዙሪያ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን ለመከላከልና ደህንነቱ የተጠበቀ የፍልሰት አማራጭን ለማበረታታት የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።
በተጨማሪም ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራው ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝ አስታዉቋል።
መጋቢት 07/2018 ዓ.ም
