በህገ ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ 6 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ።

ተጠርጣሪዎቹ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት መሳለሚያ አካባቢ ከሚገኝ አንድ የነዳጅ ማደያ ሲሆን፤ በማደያው በነዳጅ መቅዳት ሙያ ላይ የተሠማራው አሸናፊ ጥላሁን እና ሱልጣን ተክላይ የተባለ አሽከርካሪ ነው።

ግለሰቦቹ ጨለማን ተገን በማድረግ ከተጠቀሰው የነዳጅ ማደያ የቀዱትን 6 በርሜል ወይም 1200 ሊትር ነዳጅ ተሽከርካሪን በመጠቀም ጭነው ሲያዘዋውሩ በልደታ ክ/ከተማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የልደታ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ስር በማዋል ባደረገው ምርመራም ነዳጁን በህገ ወጥ መንገድ ከከተማው ክልል ለማስወጣት ሲንቀሳቀሱ እንደነበርም ገልጿል።

ወቅታዊውን ዓለማቀፉዊ ሁኔታ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጥቶበት ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባን የነዳጅ ምርት በህገ ወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ፣ ነዳጅ የሚደብቁና መሠል የወንጀል ድርጊት ውስጥ በሚገቡ የነዳጅ ማደያዎች፣ ሠራተኞችና ግለሠቦች ላይ የሚወስደውን ህጋዊ እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አሳስቧል።

መጋቢት 07/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *