ዓለም በአስርት ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ የኃይል ቀውስ ተደቅኖባታል

አሜሪካና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱትን ጥቃት ተከትሎ ኢራን ቁልፍ የሆነውን ሆርሙዝ የባህር በር ዘግታለች፡፡

ይህ ስልታዊ የንግድ መስመር በዓለም ላይ ካለው የነዳጅና የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፍላጎት 20 በመቶ የሚስተናገድበት በመሆኑ፤ውሳኔው በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ መናር አስከትሏል።

በዚህም ምክንያት የዓለም ኃይል ኤጀንሲ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብቷል፡፡

የኤጀንሲው ኃላፊ ፋቲህ ቢሮል ፤ወቅታዊው ሁኔታ ዓለምን ላለፉት አሥርት ዓመታት ታይቶ በማይታወቅ የኃይል ቀውስ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።

ቢሮል የአሁኑን ቀውስ ከ1970ዎቹ የነዳጅ እጥረት እና ከ2022ቱ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ተፅዕኖ ጋር አነጻጽረውታል።

እንደሳቸው ገለጻ፤ በአሁኑ ወቅት አለም እየተጋፈጠች ያለችው ሁለት የነዳጅ ቀውሶች እና አንድ የጋዝ አቅርቦት መቋረጥ በአንድ ላይ የተሰባጠሩበትን አስቸጋሪ ወቅት ነው።

ይህ ድርብርብ ችግር በዓለም ኢኮኖሚ ላይ የረጅም ጊዜ መዋዠቅ ሊፈጥር እንደሚችል ታምኖበታል።

ሳራ ዮሃንስ

መጋቢት 14/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *