ኢራን የትራምፕን የድርድር ንግግር ‹‹የውሸት ዜና›› በማለት ውድቅ አደረገች።

ኢራን ማክሰኞ ዕለት በርካታ ሚሳኤሎችን በእስራኤል ላይ ማስወንጨፏን ገልፃ፥የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ባለስልጣናት ጋር ውጤታማ ውይይት አድርገናል ማለታቸውንም ውድቅ አድርጋለች።

ትራምፕ ውይይት አድርገናል ካሉ በኋላ በኢራን የሃይል ማመንጫዎች እና ሌሎች የኢነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚደርሰውን የቦምብ ጥቃት ለ5 ቀናት አዘግይተዋል።

በማህበራዊ ድረ ገፃቸዉ ላይ ትራምፕ እንዳጋሩት፤አሜሪካ እና ኢራን ስለ መካከለኛው ምስራቅ ሙሉ እና አጠቃላይ የጦርነት አፈታት ዙሪያ በጣም ጥሩ እና ውጤታማ ውይይቶችን አድርገዋል ብለዋል።

በዚህም ምክንያት ትራምፕ ኢራን የሆርሙዝ ባህርን እንደገና ካልከፈተች በሚል የኢራንን የሃይል ማመንጫዎች ለመምታት የነደፉትን ዕቅድ ለአምስት ቀናት አራዝመዋል ፡፡

ይህ ጥቃት የኢራንን የኢነርጂ ጣቢያዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን፥አሜሪካ በሀገሪቱ ላይ የምታደርሰዉ ጥቃት መቀጠሉን የአሜሪካ ባለስልጣንን ጠቅሶ ሴማፎር ዘግቧል።

አሜሪካ እና እስራኤል ጦርነታቸውን በየካቲት 28 ከከፈቱበት ጊዜ አንስቶ ኢራን 20 በመቶ የሚሆነው የዓለም ዘይት እና ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ መተላለፊያ የሆነውን ቁልፍ የባህር ወሽመጥ ዘግታለች፡፡

እስካሁን በጦርነቱ ከ2 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

ሊዲያ ደሳለኝ

መጋቢት 15/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *