ስምምነት “በጣም በፍጥነት” ሊደረስ እንደሚችል ተናግረዋል።
ትራምፕ የኢራንን ነዳጅ መውሰድ እንደሚፈልጉ እና ዋናውን የነዳጅ ማዕከል ካርግ ደሴትን ሊቆጣጠሩ እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ባለስልጣናት ወታደሮቻቸው ለምድር ላይ ውጊያ እየተዘጋጁ ባለበት ወቅት ይህ የትራምፕ አስተያየት ቢመጣም፣ በሌላ በኩል ደግሞ የሰላም ስምምነት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊደረስ እንደሚችል ገልጸዋል::
ትራምፕ ትላንት እሁድ አሜሪካ በኢራን ውስጥ ለረጅም ጊዜ ሲፈለጉ የነበሩ በርካታ ኢላማዎችን መምታቷን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል እስራኤል በቴህራን ላይ አዳዲስ ጥቃቶችን እያደረሰች መሆኑን ገልጻለች።
የኢራን ፓርላማ አፈ-ጉባኤ በበኩላቸው፤የኢራን ኃይሎች የአሜሪካ እግረኛ ወታደሮች ላይ “የእሳት ናዳ ለማውረድ” እየጠበቁ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ ውጥረት ሳቢያ የነዳጅ ዋጋ ከ1መቶ15 ዶላር በላይ የናረ ሲሆን፤የማዳበሪያ ምርትን ወደ ውጭ ለመላክ አስቸጋሪ በመሆኑ የምግብ ዋጋ ሊጨምር እንደሚችል ሌላ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።
ይህ ባለበት ሁኔታ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬር ስታርመር የጦርነቱን ተፅዕኖ ለመወያየት በዳውኒንግ ስትሪት ከንግድ መሪዎች ጋር ሊገናኙ ቀጠሮ ይዘዋል።
ሀና ሰይፉ
መጋቢት 21/2018 ዓ.ም
