“በትግራይ አስቻይ ሁኔታ ባለመፈጠሩ የአጀንዳ ማሰባሰብን አዲስ አበባ ለማድረግ መወሰኑ ሽሽት አይደለም ፤ ሽሽት የሚሆነዉ አዲስ አበባ የእኛ አይደለችም ብለን ስናስብ ነዉ” ዋና ኮምሽነር መስፍን አርአያ

የትግራይ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታን በአዲስ አበባ የማካሄድ ዉሳኔን አስመልክቶ ከተሳታፊዎች ቅሬታዎችን በተቃራኒም የድጋፍ ሀሳቦችን አስተናግዷል።

ኮምሽኑ እያደረገ ባለዉ የመጀመሪያው ቀን የዉይይት መርሃግብር ሂደቱ አስመልክቶ  ተሳታፊዎች ጥያቄዎች ቀርበዋል።

አንድ በመድረኩ የተሳተፎ ግለሰብ ” ሂደቱን ለማካሄድ በትግራይ አስቻይ ሁኔታ ከሌላ በመሸሽ ነዉ ወይ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር የሚቻለዉ?” ሲሉ  ጠይቀዋል።

ሌላኛዉ ከትግራይ የመጡ ተሳታፊ ግለሰብ ” የትግራይ ህዝብ ችግር ብዙ ነዉ፤ እኛ ከክልሉ ብንመጣን ሀሳባችንን ልንገልፅ እንችላለን እንጂ ህዝብን መወከል አንችልም” ሲሉ ሀሳባቸዉን ተናግረዋል።

ተሳታፊዉ ሲቀጥሉም” ችግር ያለበት ማህበረሰብ ጋር መድረስ አለብን፤  በክልሉ ወንድማማቾች እየተጠፋፉ ያለበት ሁኔታ ላይ ነን ” ሲሉ ገልፀዋል።

ከነዚህ ዉጪ አንድ ሌላ ተሳታፊ ዛሬ በተጀመረዉ የአዲስ አበባዉ መድረክ የተገኙ ተሳታፊዎች” የትግራይ ተወላጅ መሆናቸው እርግጠኛ ነን ወይ ሲሉ?” ጠይቀዋል።

በዉይይት መድረኩ ከነዚህ ሀሳቦች በተቃራኒ ኮምሽኑ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታ በክልሉ አሰቻይ ሁኔታ እንደሌለ ተናግረዉ በአዲስ አበባ መካሄዱ ተገቢ መሆኑን ገልፀዋል።

አንዳንድ ተሳታፊዎች ለዚህ ዉይይት ወደ አዲስ አበባ ለመምጣት ችግሮች እንደገጠማቸዉ ተናግረዉ ፤ ክልሉ ዉስጥ ባለዉ ሁኔታ ኮምሽኑ ክልሉ ላይ ሂደቱን ለማድረግ እንደሚቸገርም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮምሽን ኮምሽነሮች የተነሱትን ሀሳቦች አስመልክቶ ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል።

የኮምሽኑ ምክትል ኮምሽነር ሂሩት ገ/ስላሴ በሰጡት ማብራሪያ ” ሂደቱን በክልሉ ማድረግ የእኛም ፍላጎት ነበር፤ ሆኖም በስራችን ምክንያት ሰዎችን የሚጎዱ ነገሮችን ማድረግ ስለሌለብን በአዲስ አበባ ለማድረግ ወስነናል” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ በአዲስ አበባዉ ሂደት ሊቀሩ የሚችሉት የወረዳ ተሳታፊዎች ናቸዉ ያሉት ምክትል ኮምሽነሯ እነዚህ ተሳፊዎች አንድ ሶስተኛ ያህል የተሳታፊዎች ቁጥር የሚይዙ ናቸዉ ብለዋል።

የኮምሽኑ ዋና ኮምሽነር መስፍን አርአያ በበኩላቸዉ “ሂደቱ አዲስ አበባ መደረጉ  ሽሽት አይደለም፤ ሽሽት የሚሆነዉ አዲስ አበባ ሀገራችን አይደለም ብለን ስናስብ ነዉ፤ የትም ቦታ እስካደረግነዉ ሀገራችን ላይ እያደረግን እንዳለ መታሰብ አለበት ” ብለዋል።

በተጀመረዉ የአዲስ አበባዉ መድረክ ሆነ በነበሩ ውይይቶች የአንድ ወገን ሰዎች ናቸዉ ዉይይት ያደረጉት ለሚለዉ ጥያቄም እርሱን የምታዉቁት እናንተ ናችሁ እኛ ግን አሳታፊ ዉይይት አድርገናል” ሲሉም ተናግረዋል።

ቁምነገር አየለ

መጋቢት 23/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *