“የትራንስፖርት አገልግሎት ይቆማል” በሚል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤትን ስምና ሎጎ በመጠቀም የሚሰራጨው መረጃ የተሳሳተ እና የውሸት መሆኑን እናሳውቃለን ሲል ሚኒስቴሩ አስታዉቋል።
መረጃው ውሸት ነዉ፤መንግስት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲቆም ያስተላለፈው ምንም ዓይነት ትዕዛዝ የለም። አገልግሎቱ እንደተለመደው ይቀጥላል ብሏል።
በቀጣይም ነዳጅን በተመለከተ የሚወጡ አዲስ መረጃዎች በተደራጀዉ የሁኔታዎቸ መከታተያ ልዩ ክፍል ይፋ የሚሆን መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን ሲል ገልጿል፡፡
ከማይታወቁ ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ባለማጋራት የሀሰተኛ ወሬዎችን ስርጭት በጋራ እንከላከል ሲልም መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
