ፕሬዝዳንት ፑቲን ከግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደላቲ ጋር በሞስኮ ተወያዩ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ ጋር በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት እና በኢኮኖሚ ትብብር ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።

ፑቲን በቀጣናው ያለውን ሁኔታ ለማረጋጋት ‹‹በአቅማችን ያለውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን›› ብለዋል።

አክለውም መንግስታቸው ከግብፅ ጋር የምግብ አቅርቦትን፣ በተለይም የሩሲያ እህልን በማሳደግ ረገድ እንዲሰራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን፤ ሩሲያ በምርት ሰብልም ሆነ ወደፊት በሚኖሩ አቅርቦቶች ላይ ‹‹ምንም ዓይነት ችግር የለባትም››ሲሉ ገልጸዋል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሩሲያ ለኢነርጂ እና ለምግብ ዋስትና ለምታደርገው ድጋፍ ፑቲንን ያመሰገኑ ሲሆን፤በስንዴ እና በእህል ግብይት ላይ ያለውን ቀጣይነት ያለው ትብብር ላይ ትኩረት አድርገዋል፡፡

ባድር አብደላቲ ግብፅ በጥቅምት ወር በሚካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ማቀዷን አረጋግጠው፤እስከዚያው ድረስ የቀጣናው ውጥረት ይረግባል የሚል ተስፋቸውን ገልጸዋል።

የፑቲን እና የአብደላቲ ስብሰባ የተካሄደው፤ ሞስኮ በቀጣናው ካለው ግጭት ጋር ተያይዞ በመካከለኛው ምስራቅ እና በአፍሪካ ካሉ ዋና ዋና አጋሮች ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር በምትጥርበት ወቅት ነው።

ፑቲን ሩሲያ ‹‹ሁኔታውን ወደ መደበኛ እና የተረጋጋ ደረጃ ለመመለስ››ለመርዳት ዝግጁ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

ካይሮ በበኩሏ ከሞስኮ የረጅም ጊዜ የእህል እና የኢነርጂ አቅርቦትን ለማረጋገጥ ያላትን ፍላጎት አስታዉቃለች፡፡

እስከዳር ግርማ

መጋቢት 25/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *