በነዳጅ ዋጋ መናር ምክንያት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ፤ ለሦስት ወራት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በዛምቢያ ተግባራዊ ይሆናል።
ፕሬዝዳንት ሃካይንዴ ሂቺሌማ በቤተ-መንግሥት በጠሩት ልዩ የካቢኔ ስብሰባ፤ በቤንዚንና በናፍጣ ላይ ይጣል የነበረው የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) እና የትራንስፖርት ቀረጥ ለጊዜው እንዲታገድ ተወስኗል።
እነዚህ አጭር ጊዜያዊ እርምጃዎች የታለሙት በመካከለኛው ምስራቅ በቀጠለው ግጭት ምክንያት የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተጽዕኖ ለመቀነስ ነው።
መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
