በኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፖርት ሥነምኅዳርን ለማጠናከር እየሠራ መሆኑን ያንጎ አስታወቀ

የዓለም አቀፉ ቴክኖሎጂ ኩባንያ፣ ያንጎ ግሩፕ አካል የሆነው ያንጎ ኢትዮጵያ፣ ለአጋርነት አቅም እና ፍላጎት ላላቸው አካላት በስካይላይት ሆቴል የተሳትፎ ዝግጅት አካሄደ፡፡ በዝግጅቱ ላይም፣ የንግድ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ባለሀብቶች እና የንግድ ባለቤቶች የተሳተፉ ሲሆን ተፈላጊነቱ እና አገልግሎቱ እየተስፋፋ ባለው የዲጂታል ትራንስፖርት ሥነምኅዳር ውስጥ ያሉ ምቹ የሽርክና እድሎችን መርምረዋል።

በዝግጅቱ ላይ ያንጎ ሦስት የሽርክና ሞዴሎችን ያስተዋወቀ ሲሆን ሞዴሎቹም፣ አሽከርካሪ በማፈላለግ እና በማኅበረሰብ አስተዳደር ላይ የሚያተኩረው አገናኝ (Connector) ሞዴል፣ ባለሀብቶች የራሳቸውን ተሽከርካሪዎች እንዲያስተዳድሩ እና እንዲቆጣጠሩ የተነደፈ የትራንስፖርት አጋርነት (Fleet Partner) ሞዴል እና የትራንስፖርት አገልግሎትን በማስተዳደር በተመሳሳይ ጊዜ የተለያዩ አሽከርካሪዎችና ተገልጋዩን ማኅበረሰብ ግንኙነትን በማስፋት ሁለቱንም አቀራረቦች የሚያጣመር ሃይብሪድ (Hybrid) ሞዴል ናቸው። 

ያንጎ፣ ተለዋዋጭና ሊስፋፋ የሚችል የሽርክና ሥነምኅዳር በመፍጠር ለኢንተርፕረነርሺፕ ድጋፍ እንዲሰጥ እና ነጋዴዎች በኢትዮጵያ እየደገ ባለው የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ዘርፍ ውስጥ እንዲሳተፉ የሚያበረታታ አቀራረብን አሳይቷል፡፡

ይህ ዝግጅት በኢትዮጵያ ካሉ ሀገራዊ ንግዶች ጋር የሽርክና ተባባሪነትን ለማጠናከር እና የተስፋፋና ተስማሚ የትራንስፖርት አገልግሎት ኔትወርክ ለማቋቋም ያንጎ ከሚያደርጋቸው የማስፋፊያ ጥረቶች ውስጥ የሚመደብ ነው።

ሚያዚያ 01/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *