7ተኛውን ዙር ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት በዚህ ወቅት የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ላይ መካሄዱን ቀጥሏል፡፡
የኢትዮጲያ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምርጫው ላይ በሙሉ አቅማችን እየሰራን እንዳልሆነ ይሰማኛል ነገር ግን አስቻይ ሁኔታ ተፈጥሮ ምርጫው ፍትሀዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ እንፈልጋለን ሲል ትብብር ለኢትዮጲያ አንድነት ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
የትብብር ለኢትዮጲያ አንድነት ተወካዩ መምህር አብረሃም ሃይማኖት ለኢትዮ ኤፍኤም እንዳስታወቁት ፓርቲው በቅስቀሳ ወቅት እስካሁን ያጋጠመው ችግር እንደሌለ ነግረውናል፡፡
ኢዜማ በበኩሉ አልፎ አልፎ በተለያዩ አካባቢዎች በገዢው መንግስት በኩል ባሉ ካድሬዎች ከሚፈጥሩ ወከባዎች ውጪ እስካሁን በቅስቀሳ ወቅት የከፋ ችግር አልገጠመንም ሲሉ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ እዩኤል ሰለሞን ነግረውናል::
በተመሳሳይ ህዳሴ ፓርቲ የአደባባይ የይምረጡኝ ቅስቀሳውን እያካሄደ መሆኑን አስታውቆ ያጋጠመው አሉታዊ ችግር አለመኖሩን ለጣቢያችን ነግሮናል፡፡
47 የፓለቲካ ፓርቲዎችን እና ከ 70 በላይ የግል እጩ ተወዳዳሪዎችን የሚያሳትፈው የሰባተኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ ከ 46 ሚለየን በላይ ዜጎች የመራጭነት ካርድ እንደወሰዱ እየተነገረ ይገኛል፡፡
የውልሰው ገዝሙ
ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም
