የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግስት ከ2መቶ በላይ ማህበራትን አፈረሰ

ይህች የሳህል ቀጣና ሀገር በአጠቃላይ በጤና፣ በትምህርት፣ በሴቶች መብት፣ በግብርና፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በባህልና በስፖርት ዘርፎች ላይ የተሰማሩና ዋና መሠረታቸውን ቡርኪና ፋሶ ያደረጉ 2መቶ5 ማህበራትን አግዳለች።

በ2022 በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ከያዘ ወዲህ ገዥው ወታደራዊ መንግስት፤በመቶዎች በሚቆጠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ፣ በሠራተኛ ማህበራት፣ በመሰብሰብ ነፃነት እና በወታደራዊ አገዛዙ ላይ በሚነሱ ተቃውሞዎች ላይ እርምጃ ሲወስድ ቆይቷል።

በሐምሌ 2025 የወታደራዊዉ መንግስት መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ የመብት ተሟጋች ቡድኖችን እና ማህበራትን አሠራር የሚገድብ ሕግ ፈርመዋል።

መንግሥት ባወጣው አዋጅ “በዕገዳው ወቅት ማህበራቱ ሕጉን እያከበሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የታለሙ ተግባራት ብቻ ይፈቀዳሉ” ብሏል።

የውጭ ዕርዳታ የሚቀበሉ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የበጎ አድራጎት ተቋማት፣ ከሠራዊቱ ጋር ከሚዋጉ ጂሃዲስቶች ጋር በማበር ወይም በስለላ ተግባር በጁንታው በተደጋጋሚ ይወነጀላሉ።

ባለፈው ሚያዝያ ወር የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ ባለሥልጣናት በመቶዎች የሚቆጠሩ ማህበራትን አብዛኞቹ በሰብአዊ መብት ሥራ ላይ የተሰማሩ በመላ ሀገሪቱ እንዳይንቀሳቀሱ አግደው ነበር።

በዚያው ወር ሂውማን ራይትስ ዎች፤ ሕጉ ወታደራዊዉ መንግስት በሲቪል ማህበረሰቡ ላይ የሚወስደውን አጠቃላይ ጭቆና እንዲያጠናክር አስችሎታል ሲል ገልጿል።

እስከዳር ግርማ

ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *