ኩባንያዉ ከመጋቢት 23 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ያለውን የሥራ አፈፃጸም አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዊም ቫንሄሌፑቴ የ15.9 ቢሊየን ብር ዓመታዊ ገቢ መገኘቱን ገልጸዉ፤ይህ የገቢ መጠን ኩባንያው ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ1መቶ30.9 በመቶ ከፍተኛ እድገት ማስመዝገቡን ያሳያል ብለዋል።
እንደ ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ገለጻ ለዚህ የገቢ እድገት በዋናነት አስተዋጽኦ ያደረጉት የቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር መጨመር፣ በሞባይል ዳታ አገልግሎት ላይ የታየው ከፍተኛ ፍላጎት እና የኤም-ፔሳ የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ቁጥር ማደግ ናቸው።
በበጀት ዓመቱ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የ90 ቀናት ንቁ ደንበኞች ቁጥር 13.6 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን፤ ይህም የ54.2 በመቶ እድገት አሳይቷል ነዉ የተባለዉ፡፡
የሞባይል ዳታ አገልግሎት 9.6 ቢሊየን ብር በማስገኘት ቀዳሚውን ድርሻ በመያዝ የኩባንያው ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሳፋሪኮም የኔትወርክ መሠረተ ልማቱን በማስፋፋት በአሁኑ ወቅት 59.2 በመቶ ለሚሆን ህዝብ የ4G ኢንተርኔት አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጿል።
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እስካሁን ባለው ሂደት በሀገሪቱ ውስጥ በአጠቃላይ የ2.6 ቢሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ያከናወነ ሲሆን፤ ይህም ለኔትወርክ መስፋፋያና ለሥራ ዕድል ፈጠራ መዋሉ ተጠቁሟል።
ኢትዮጵያ ለጥቅል የኩባንያው ገቢ የ15 በመቶ አስተዋፅኦ ማበርከቷንና ይህም በኩባንያው የ2030 ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ውስጥ ያላትን ጉልህ ሚና እንደሚያሳይ ዋና ስራ አስፈጻሚዉ ገልጸዋል፡፡
እስከዳር ግርማ
ግንቦት 03/2018 ዓ.ም
