የአሜሪካ እና የፈረንሳይ ዜጎች በሀንታ ቫይረስ  መያዛቸው ተረጋገጠ።

ገዳይ በሆነው የሀንታ ቫይረስ ወረርሽኝ ከተመታች የመንገደኞች መርከብ ወጥተው ወደ ሀገራቸው የተመለሱ አንድ አሜሪካዊ እና አንድ የፈረንሳይ ዜጋ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡን ባለስልጣናት ገለጹ።

የአሜሪካ የጤና መምሪያ በበኩሉ፣ በዚሁ የሀገር መመለሻ በረራ ላይ የነበሩ ሌላ ሁለተኛ አሜሪካዊ ዜጋም መጠነኛ ምልክቶች እንደታዩባቸው ገልጾ፤ ሁለቱም መንገደኞች ተላላፊ ለጥንቃቄ ሲባል  በሽታን በሚከላከሉ (በባዮ-ኮንቴይመንት)  ክፍሎች ውስጥ ሆነው መጓዛቸውን አክሏል።

የፈረንሳይ ጤና ሚኒስትር እስቴፋኒ ሪስት  እንደተናገሩት፣ አንዲት ሴት በፓሪስ ተገልላ ትገኛለች፤ የጤና ሁኔታዋም እየተባባሰ ነው።

ከዚሁ ጋር ተያይዞም ከእሷ ጋር ንክኪ ነበራቸው የተባሉ 22 ሰዎች ተለይተዋል፤በአሁኑ ወቅት በስፔን የካናሪ ደሴቶች ቆማ በምትገኘው ኤምቪ ሆንድየስ (MV Hondius) መርከብ ላይ ከነበሩት መንገደኞች መካከል ከ90 በላይ የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው በመመለስ ላይ ናቸው።

በመርከቧ ላይ ተጉዘው ከነበሩ ሶስት መንገደኞች ጥንድ ሆላንዳውያን እና አንዲት ጀርመናዊት  ህይወታቸው አልፏል። ከእነዚህ ውስጥ ሁለቱ በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ይሁን እንጂ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) አንዳንድ የሆላንድ መርከብ መንገደኞች በደቡብ አሜሪካ ሳሉ ሳይዙት አልቀሩም ተብሎ የሚታመነው የአንዴስ (Andes) ዝርያ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፍ እንደሚችል ተገልጿል።

ባለስልጣናት እንደሚሉት ከሆነ ከፍተኛ የሆነ ወረርሽኝ የመከሰቱ ዕድል በጣም ዝቅተኛ ነው፤ የአሜሪካ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ሰኞ ማለዳ ላይ ባወጣው መግለጫ፣ በበረራው ላይ የነበሩት 17ቱም የአሜሪካ ዜጎች በነብራስካ በሚገኝ የህክምና ተቋም “ክሊኒካዊ ግምገማ” ይደረግላቸዋል፤ሌሎች ሰባት አሜሪካውያን መንገደኞች ቀደም ብለው የተመለሱ ሲሆን፣ በሚኖሩባቸው ግዛቶች ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የአሜሪካው በሽተኛ መኖሩ ከመረጋገጡ በፊት፣ የዓለም ጤና ድርጅት ኃላፊ ቴዎድሮስ አድሃኖም  አሜሪካ የድርጅቱን መመሪያ ላለመከተል የወሰነችው ውሳኔ “አደጋ ሊኖረው ይችላል” ሲሉ አስጠንቅቀው ነበር።

የበሽታው ምልክቶች ትኩሳት፣ ከፍተኛ ድካም፣ የጡንቻ ህመም፣ የሆድ ህመም፣ ማስታወክ፣ ተቅማጥ እና የትንፋሽ ማጠርን ሊያካትቱ ይችላሉ።

ሀና ሰይፉ

ግንቦት 03/2018 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *